ለወደቀው እግር ኳሳችን አንድ መፍትሔ ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ
ነሐሴ 11, 2008

ለወደቀው እግር ኳሳችን አንድ መፍትሔ ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ

በይርጋ አበበ

የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ ልኳል። ክለቡ ለፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ ላይ ሁሉም የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እንዲደርሳቸውና እንዲመለከቱት የሚል ግልባጭ ስላከለበት በዚህ ጽሁፍ የክለቡን ደብዳቤ ይዘት ለመመልከት ወደድን።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ በግምትና በዘፈቀደ የሚመራ ብቸኛ ዘርፍ ነው ቢባል መዋሸት አይሆንም። እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በስሩ ከወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ጀምሮ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ፣ ሱፐር ሊግ፣ ብሔራዊ ሊግ እና ከ17 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን የሚያካሂድ ቢሆንም አንዱንም በተገቢው መንገድ ሲመራው አይታይም። ለዚህ ደግሞ ችግሩ የፌዴሬሽኑ የሰው ሀይል ብቃት አነስተኛ መሆንና የስራ አስፈጻሚዎቹ በተለይም ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው ብቃታቸው አነስተኛ በመሆኑ ነው።

የደደቢት እግር ኳስ ክለብም በቀጣዩ የውድድር ዓመት ፕሪሚየር ሊጉ መቼ ተጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ የጊዜ ሰሌዳውን አሳውቁን። አለዚያ እኛ ክለቦቹ ለማለት ነው በዘፈቀደ እየተመራን ላላስፈላጊ ወጪ፣ ድካም እና የጊዜ ብክነት እየተጋለጥን ነው። ይህን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ የብቃት ማነስ ካለበት ክለባችን ከጎኑ ሆኖ ድጋፍ ሊሰጠው ዝግጁ ነው ሲል አስታውቋል።

ከዜናው ጋር አብረን አያይዘን የምንገልጸው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ደብዳቤ “እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ዘንድሮም የ2009 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሃ ግብርን ፌዴሬሽኑ ስላላሳወቀን የዝግጅት ስራዎቻችንን በግምትና በደመነፍስ እንድናካሂድ ልንገደድ ነው። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ ክለቦች በእቅድ እንዲመሩ እንቅፋት ከመሆን ይልቅ ድጋፍ እንዲያደርግና አመራር እንዲሰጥ እንጠይቃለን” ብሏል።

በአንድ አገር እግር ኳስ የውስጥ ሊግ ውድድር ከመካሄዱ ቢያንሰ ሁለት እና ሶስት ወራት ቀደም ብሎ መቼ እንደሚጀመር ከውድድሩ አዘጋጅ ይገለጻል። ይህ መሆኑ ደግሞ ክለቦች ለውድድር ምን ያህል ሳምንት ሲቀራቸው ወደ ዝግጅት እንዲገቡ እና ቡድናቸውንም በምን ያህል ደረጃ ማዋቀር እንደሚኖርባቸው በግልጽ ያሳውቃልና ለክለቦቹ ተስማሚ አሰራር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ውድድሮቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተጀምረው ሲጠናቀቁ ክለቦች ካላስፈላጊ ወጪ እና ከጊዜ ብክነት የሚድኑ ከመሆኑም በላይ ተጫዋቾች የብቃት መውረድና የጉዳት ስጋት እንዳይደርስባቸው ይረዳቸዋል።

ይህን መገንዘብ ያልቻለው ወይም ደግሞ ቢገነዘብም እንኳን መስራት ያልቻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን ዘንድሮም እንዳለፉት ዓመታት ድክመቶቹ የቀጣዩን ዓመት የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መቼ እንደሚጀመር ለማሳወቅ እንኳን አቅም ያለው አልመሰለም። ይህን የደደቢትን ጥያቄም ሌሎች ክለቦች በሚገባ ሊመለከቱትና ፌዴሬሽኑም ራሱን ሊፈትሽበት የሚገባ ድርጊት ነው። አለዚያ ምንም ባልተሰራበት እግር ኳስ ላይ ከብሔራዊ ቡድን ውጤት መጠበቅ የዋህነት ነው የሚሆነው።

Dedebit Letter to EFF
Dedebit Letter to EFF
Dedebit Letter to EFFethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!