ሀዋሳ ከነማ ቶጓዊ ፕሮፌሽናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ነሐሴ 18, 2008

ሀዋሳ ከነማ ቶጓዊ ፕሮፌሽናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ

 ደቡብ አፍሪካዊውን ብሪያን ኦበቤጎን ያሰናበተው እና ዮሃንስ በዛብህን ለኢትዮጵያ ቡና አሳልፎ የሰጠው የውበቱ አባተ ቡድን ሀዋሳ ከነማ ቶጓዊ ግብ ጠባቂ ማስፈረሙ ታወቀ።

አዲሱ የሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት  ቶጎ  ሲውዲን ፡ጋቦን .አፍሪካ ሊጎች ላይ ተጫውቶ ማሳለፉን የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ከሃዋሳ ገልጸውልናል።

በክለቡ የስራ ኃላፊዎች ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ሮበርት ኦዶንካራ ጋር ያነጻጸሩት አዲሱ ቶጓዊ ግብ ጠባቂ ስሙ ማኑዌል ሱሆሆ ሜንሳ ሲሆን ለሃገሩ ቶጎ ብሔራዊ ቡድን 17 ዓመት በታች 19 በታች እና 20 ዓመት በታች ተጨውቷል። በአሁኑ ወቅትም የብሔራዊ ቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ እንደሆነ ተነግሮለታል። በተያያዘ ዜና በአጥቂ ስፍራ ላይ ክፍተት ያለበት ሃዋሳ ከነማ አብይ ምገስን ለማስፈረም ያደረገው ሙከራ  በግል ችግር ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

በዚህ የተነሳም አንድ ሁነኛ አጥቂ ከጋና ለማምጣት ጥረት ላይ መሆናቸውን የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር አለም ባንተ ማሞ አያይዘው ገልፀዋል። የያሬድ ዝናቡ ጉዳይም በክለቡ የሙከራ ጊዜ እንደተሰጠው እንጂ በይፋ እንዳልፈረመ ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል። ሃዋሳ ከነማ በዝውውር መስኮቱ  ፍሬው ሰለሞንን እና ዮናታን ከበደን አስቀድሞ ያስፈረመ ሲሆን ሰባት ልጆችን ደግሞ ከታችኛው ቡድን አሳድጓል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!