የፕሪሚየር ሊጉ ተወዳዳደሪዎች ለዝግጅት ሀዋሳን መርጠዋልየፕሪሚየር ሊጉ ተወዳዳደሪዎች ለዝግጅት ሀዋሳን መርጠዋል
ነሐሴ 18, 2008

የፕሪሚየር ሊጉ ተወዳዳደሪዎች ለዝግጅት ሀዋሳን መርጠዋል

አወዛጋቢውና አያምርብሽ የሚባለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ 16 ክለቦችን በመያዝ መስከረም መጨረሻ ላይ እንደሚጀመር ታውቋል

በውድድሩ ላይ ተካፋይ የሚሆኑትክለቦችም ዝግጅታቸውን እያካሄዱ መሆኑ ታውቋል ኢትዮጵያ ቡናኢትዮጵያ ንግድ ባንክድሬዳዋ ከተማሲዳማ ቡናመብራት ሀይል እና የሁለት ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሀዋሳ ከነማ እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ዘንድሮም ለዝግጅት ሀዋሳን መርጠው ዝግጅታቸውን ጀምረዋል

ልምምዳቸውንም ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ሜዳዎች መካከል ደቡብ አካዳሚግብርና ኮሌጅአርቴፊሻል፣ በዋናው ዩኒቨርሲቲ እና በአዲሱ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ላይ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከነማ አዳማ ላይ ዘንድሮ ሲዘጋጁ ሊጉን የተቀላቀሉት ወልድያ ከተማና ፋሲል ከነማ አዲስ አበባ ላይ እንዲሁም አባቡና ጅማ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ቢሾፍቱ ላይ የዝግጅት ልምምዳቸውን እንደሚሰሩ ታውቋል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!