ማራቶኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹን ከጋቦኑ ጉዞ ውጪ አድርጎ ዛሬ ይጠናቀቃል
ነሐሴ 29, 2008

ማራቶኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹን ከጋቦኑ ጉዞ ውጪ አድርጎ ዛሬ ይጠናቀቃል

በይርጋ አበበ

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ተደልድሎ የማጣሪያ ጨዋታዎቹን ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት የሲሼልስ አቻውን ሁለት ለአንድ ቢያሸንፍም በአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳትፈውን ውጤት ማግኘት አልቻለም።

ለእያንዳንዱ የማጣሪያ ጨዋታዎች ረጅም የልምምድና የዝግጅት ጊዜ ሲያጠፋ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በስድስት ጨዋታ 11 ነጥብ ይዞ 16 ነጥብ ካላት የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ ቢያገኝም ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ማለፍ እንዳይችል ተደርጓል። ብሔራዊ ቡድኑ ለዚህ የበቃው ደግሞ በመጀመሪያዎቹ አራት የምድቡ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሰበሰበው ነጥብ አምስት ብቻ ስለነበረ ነው። በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ሲሰለጥን የቆየው ብሔረቀዊ ቡድኑ አንድ ብቻ አሸንፎ ሁለት አቻ ወጥቶ በአንዱ ደግሞ በሰፊ የጎል ልዩነት በመሸነፉ አሁን ለደረሰበት ውድቀት ተጠያቂ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ዮሃንስን በውጤት ማጣት ምክንያት ከኃላፊነቱ ያነሳው ፌዴሬሽኑ በዮሃንስ ምትክ ገብረመድኅን ኃይሌን ከቀጠረ በኋላ ሁለት ተከታታይ የምድቡን የማጣሪያ ጨዋታዎች አካሂዶ ሁለቱንም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዚህም ሁለት ጨዋታ ስድስት ነጥብ እና ተጨማሪ ሁለት ጎሎችን ቢያገኝም ቀደም ሲል የነበረበት አምስት የጎል እዳ ቡድኑ ከጋቦኑ ውድድር ውጪ እንዲሆን ተገድዷል።

ዋልያዎቹ ትናንት አመሻሹ ላይ በሀዋሳው ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያካሄዱትን ጨዋታ በርካታ ደጋፊ በስታዲየም ተገኝቶ የተከታተለው ሲሆን በውጤቱም ሲሸልሶች መሪ መሆን ችለው ነበር። ሆኖም ጌታነህ ከበደ እና ሳላዲን ሰይድ በተከታታይ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችለውታል። ጌታነህ ከበደ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ስድስት ጎሎችን በማስቆጠር የማጣሪያው ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ አጠናቋል።

 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
SITOTAW [223 days ago.]
 best

Orisa Bokaansa [220 days ago.]
 Waaliyawoochu

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!