ሉሲዎቹ በነሃስ ሜዳሊያ ሲመለሱ ፕሪሚየር ሊጉ ጥቅምት 20 እንደሚጀመር ተገልጿል
መስከረም 11, 2009


በካሳ ሀይሉ

ሩዋንዳ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ወይም ሴካፋን አዘጋጅታ ነበር። ሩዋንዳ ባዘጋጀችው የሴቶች የምስራቅ አፍሪካ አገራት ውድድር ለአሸናፊው ጉርሻ ለተሸናፊው ደግሞ ሽረት ባይኖረውም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ተሳትፎ የነሃስ ሜዳሊያ ይዞ ተመልሷል። በውድድሩ ስምንት ጎል ያገባው የመሰረት ማኔ ስብስብም የደደቢቷን ሎዛ አበራን የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ አድርጎ ሲያስመርጥ በውድድሩም አምስት ጎሎችን አስቆጥራለች። ቡድኑ ዛሬ ምሳ ሰዓት ላይ አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል። ውድድሩን ታንዛኒያ በበላይነት አጠናቃለች።


በሌላ ዜና ለ2017 ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባማኮ ላይ በማሊ ብሔረዊ ቡድን ሁለት ለባዶ ተሸንፎ ተመልሷል። የመልሱ ጨዋታም ከአስር ቀናት በኋላ ድሬዳዋ ላይ ወይም ሀዋሳ ላይ የሚካሄድ ይሆናል። በአሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ የሚመራው ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ ማጣሪያው የግብጽ አቻውን በደርሶ መልስ አምስት ለሁለት አሸንፎ ማለፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2009 ዓ.ም የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የሚመጀርበትን ቀን መቁረጥ የከበደው ይመስላል። ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ ፕሪሚየር ሊጉ መስከረም 29 እንደሚጀመር አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በአንድ ጀምበር ፕሮግራሙ ወደ ጥቅምት 20 እንዲዘዋወር ማድረጉን አስታውቋል። ይህን በተመለከተ እና ያለፈውን ዓመት ውድድር ግምገማ አስመልክቶም ነገ መስከረም 12 ቀን በካፒታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ደብዳቤ አስታውቋል። በእለቱም የሊጉ ፕሮግራም እጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ይካሄዳል።  

በየዓመቱ ወጥ በሆነ የውድድር ስርዓት የማይካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለወትሮው 14 ክለቦች እየተሳተፉበት ውድድሩ የሚጠናቀቀው ሰኔ መጨረሻ ወይም ሀምሌ አጋማሹ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ዘንድሮ ደግሞ 16 ክለቦች እንዲሳተፉ ተደርጎ እያለ የውድድሩ መጀመሪያ ጊዜ ከወትሮው በተለየ መልኩ መራዘሙ የውድድሩን መጠናቀቂያ ጊዜ ወደ ኋላ እንዳይጎትተው ተሰግቷል። በአገሪቱ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሲታከልበት ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉን ውድድር በዚህ ዓመት እንዴት ሊካሄድ እንደሚችል አሳሳቢ መሆኑን በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች የሚገልጹት ሃሳብ ሆኗል።

 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
idilu [454 days ago.]
 ithiopia berawi leagi

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [63 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [63 days ago.]
 arachni_text

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!