home
About Us
Player Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Mulugeta Mherete Hawassa
Hawassa City

 
Name: Mulugeta Mherete  
Weight: 76  
Age: 00  
Height: 1.86  
Position: MF  
Club: Hawassa City  
 
 ሙሉጌታ ምህረት 

ስም ፡ሙሉጌታ ምህረት 
የሚጫወትበት  ክለብ ፡ ሐዋሳ ከነማ 
የሚጫወትበት ስፍራ ፡አማካይ 
የማልያ ቁጥር ፡ 17 
ከዚህ ቀደም የተጫወተባቸው፡- 
   19993 - 1997 ሃዋሳ ከነማ 
   1998 - 1999 ቅ/ጊዮርጊስ 
   2000 -  2001 ሃዋሳ ከነማ 
   2002-  2006 ደደቢት 
   2007 -    ሃዋሳ ከነማ ሙሉጌታ ምህረት በአሁኑ ወቅት ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ እየተጫወተ ያለ የእግር ኳስ ተጫዋች ነው፡፡ የክለቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም አምበል ነው፡፡

የልጅነት ጊዜ

ሙሉጌታ ምህረት የተወለደው በደቡብ ክልል መዲና ሀዋሳ በተለምዶ ኮረም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ወቅቱም 1977 ዓ/ም ነው፡፡ ሙሉጌታ በሀዋሳ ከተማ ህዝብ ዘንድ ሙሉዬ በሚለው ቅፅል ስም ይታወቃል፡፡ የሙሉዬ የእግር ኳስ ህይወት የሚጀምረው በተወለደበትና ባደገበት አካባቢ ባለው ኮረም ሜዳ ተብሎ በሚጠራው የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ነው፡፡ ይህ ሜዳ አዳነ ግርማ፣ በሀይሉ ደመቀ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ዮናታን ከበደ፣ ደረጀ እና ሌሎችም በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ክለቦች ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ያፈራ ሜዳ ነው፡፡

ሙሉጌታ በኮረም ሜዳ ያዳበረው የእግር ኳስ ክህሎት በ 1992 ዓ/ም በሀዋሳ ከነማ ወጣት ቡድን እንዲካተት አስቻለው፡፡ በወጣት ቡድኑ ለአንድ አመት ከተጫወተ በኃላ ወደ ዋናው ቡድን አደገ፡፡ በወቅቱ አዳነ ግርማና በሀይሉ ደመቀ የመሳሰሉት ተጫዋቾችም አብረውት ያደጉ ሲሆን ክለቡ በርካታ ተጫዋቾቹ ወደ ተለያዩ ክለቦች ተዛውረውበት ስለነበር ወጣቶችን እነ ሙሉጌታ ለምትክነት ተጠቀሙ፡፡

የዋናው ቡድን ቆይታ  

&#47761993 እና 94 በዋናው ቡድን ውስጥ በቋሚነት የተሰለፈው ሙሉጌታ ምህረት በ 1995 የቡድኑ አምበልነት ማእረግ ተሰጠው 1996 በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ሀዋሳ ከነማና ሙሉጌታ ምህረት የተለየ ታሪክ ያስመዘገቡበት ዓመት ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ክለቦች መብራት ሀይልና ቅ/ጊዮርጊስ ውጭ ማንም የክልል ክለብ እስከዚህ ወቅት ድረስ ዋንጫ ወስዶ አያውቅም ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ግን ሀዋሳ ከነማ ሻምፒዮን በመሆን የተለየ ታሪክ ሰራ፡፡ የቡድኑ መሪ የነበረው ሙሉጌታ ምህረትም ከክልል ክለብ ተጫዋቾች የመጀመሪያ የፕሪሚየርሊጉን ዋንጫ ያነሳ አምበል ለመሆን በቃ፡፡ ለሃዋሳ ከነማ ውጤታማነት ግንባር ቀደሙን ሚና የተወጣው ሙሉጌታ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎም ተመረጠ፡፡ 

ሙሉጌታ እነዚህን ክብሮች ካገኘ በኃላ በቀጣይነት በሀዋሳ ከነማ የቆየው ለአንድ አመት ተኩል ነው፡፡ በ 1998 ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተዛወረ፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታው በአብዛኛው በቋሚ ተሰላፊነት ተመራጭ ባይሆንም ተቀይሮ እየገባ ያሳይ የነበረው እንቅስቃሴ የደጋፊውን ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ ለሁለት አመት በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው ሙሉዬ በ 2000 ዓ/ም ወደ አሳዳጊ ክለቡ ሐዋሳ ከነማ በመመለስ ለሁለት  አመት ተጫወተ፡፡ በ 2002 ዓ/ም ከሀዋሳ ከነማ የወቅቱን የተጫዋች ዝውውር ገንዘብ ሪከርድ በሰበረ ሁኔታ በ 120,000 ብር ወደ ደደቢት ተዛወረ፡፡ ደደቢት በወቅቱ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማለፍ በሶስት ክለቦች መካከል ይደረግ በነበረው የአንድ ዙር ውድድር በመሳተፍ ትራንስ ኢትዮጵያንና ኒያላን በማሸነፍ ፕሪሚየር ሊጉን ሲቀላቀል ሙሉጌታ ገና ከመጀመሪያ ጨዋታው ጀምሮ አምበል በመሆን ቡድኑን በመምራት ላይ ነበር፡፡  

ብሔራዊ ቡድን 

ሙሉጌታ ምህረት ለብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠራው በ 1997 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ተካሒዶ በነበረውና በኢትዮጵያ ሻምፒዮንነት የተጠናቀቀው 28ኛው የሴካፋ ሲንየር ቻሌንጅ ካፕ ነበር፡፡ በአስራት ሀይሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጠው ሙሉጌታ በተወሰኑ ጨዋታዎች ተቀይሮ በመግባት ውጤታማ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ በዚሁ አመት በሰውነት ቢሻው ይሰለጥን በነበረው ወጣት ቡድን ተጠርቶ ተጫውቷል፡፡ 

በቀጣይ አመት 1998 በሩዋንዳ በተካሔደው 29ኛ የሴካፋ ውድድር ሻምፒዮን የሆነው የሰውነት ቢሻው ቡድንም አባል ነበር፡፡ በሁለቱም ውድድሮች የተሳተፈ ተጫዋቾች ከሼህ መሐመድ አላህሙዲ የተበረከተላቸው የ 100,000 ብር ካገኙ ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ 

በ 1999 ዓ/ም ውድድሩ አዲስ አበባ ላይ በድጋሚ ሲስተናገድ ደግሞ የሀገሩን ማልያ የመልበስ እድል አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ በተጋባዥዋ ዛምቢያ ተሸንፋ ለፍፃሜ ሳታልፍ ቀርታለች፡፡

ኢትዮጵያ ለአንጎላው 28ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ሞሪሺየስና ሩዋንዳ ተደልድላ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ባደረገች ጊዜም ሙሉጌታ ምህረት የአሰልጣኝ አብርሀም ተክለሀይማኖት ተመራጭ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር መካከል የተፈጠረ ውዝግብ ፊፋ ኢትዮጵያ ላይ እገዳ መጣሉ ቡድኑ ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶታል፡፡

በ 2002 የፊፋ እገዳ መነሳቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር ስትመለስ የመጀመሪያ ተሳትፎዋ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የተካሔደው 33ኛው የሴካፋ ውድድር ነበር ሙሉጌታ ምህረት በዚህ ውድድር ላይም የቡድኑ ዋና አምበል ሆኖ ነበር ወደ ናይሮቢ ያቀናው፡፡

ሙሉጌታ አምበልነት

ሙሉጌታ ምህረት ጥሩ ስነምግባር እንዳላቸው ከሚነገርላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ ሙሉጌታ ወደ ሀዋሳ ዋናው ቡድን ካደገበት ጊዜ ጀምሮ የአምበልነት ሃለፊነት በየሄደበት ይሰጠዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የደደቢት አምበል ሲሆን የብሔራዊ ቡድኑም አምበል በመሆን በማገልገል ላይ ነው፡፡

ethiofootball.com

 
 
 
 
 
 
 
Goal Statistics
During the match Goal
St.George Vs Hawassa City 1
Total 1
Hawassa City Players Goal Statistics
Mulugeta Mherete 1
Amele Michias 1
Gadisa Mebrat 8
Firew Solomon 10
Tafesse Solomon 2
Medhane Tadese 1
2
Desta Yohanse 2
Firdawok Sisay 3
Haymanot Worku 1
Jako Arefat 12
 
 
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro