home
About Us
Player Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Tafesse Tesfaye Adama
Adama City

 
Name: Tafesse Tesfaye  
Weight: 70  
Age: 00  
Height: 1.71  
Position: CS  
Club: Adama City  
 
ታፈሰ  ተስፋዬ 

የሚጫወትበት ክለብ:   ሐዋሳ ከነማ
የሚጫወትበት ስፍራ:  አጥቂ
ያገኛቸው ክብሮች:  ኮከብ ግብ አግቢ 1997 እና 2001, ኮከብ ተጫዋች 2000

ታፈሰ ተስፋዬ በቅርብ አመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ጎልተው ከሚታዩ ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጊዜ ኮከብ ግብ አግቢ አንድ ጊዜ አንድ ጊዜ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥም ከ  1997 ጀምሮ ያለማቋረጥ ተመርጦ እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ታፈሰ በተለይ በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ አምበል ከመሆኑ ባሻገር የቡድኑ ልዩ ምልክት ተደርጎ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡

ታፈሰ ተስፋዬ ጥቅምት 22 ቀን 1978 ዓ/ም አዲስ አበባ ሽሮሜዳ አካባቢ ነው የተወለደው፡፡ ታፈሰ የሽሮሜዳ አካባቢ ልጅ እንደመሆኑ ለእግር ኳስ ቅርብ የሆነው ገና ከህፃንነቱ ነው፡፡ በሽሮሜዳ ከሰፈሩ ልጆች ጋር የጨርቅ ኳስ ይጫወት የነበረው ትንሹ ታፈሰ ከሌሎች እኩዬቹ ጋር ጎልቶ የሚታይና እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር፡፡  በ 1992 የእግር ኳስ ፕሮጀክት ስልጠናን ተቀላቀለ፡፡ ከአንድ አመት ስልጣን በኃላ  በ 1993 የመብራት ሀይል ሁለተኛ ቡድን EEPCO B ተቀላቀለ፡፡ የክለብ ህይወቱንም አሀዱ አለ፡፡ 

የክለብ ህይወት  

 በ 1993 ዓ/ም መብራት ሀይል የሀገሪቱን ሦስት ዋንጫዎች በሙሉ ጠቅልሎ ሲወስድ የክለቡ ሦስተኛ ቡድን አባል የነበረው ታፈሰ አንድ ቀን የዋናው ቡድን ተሰላፊ ሆነ ውጤታማ እንደሚሆን ተስፋ ያደርግ ነበር፡፡ ኮከብ ግብ አግቢ እንደነበረው ዮርዳኖስ አባይ አንድ ቀን ስኬታማ እንደሚሆን ተስፋ ያደርግ ነበር፡፡ በቀጣዩ አመት 1994 የዋናው ቡድን አባል ሆነ፡፡ እስከ 1997 ዓ/ም በመብራት ሀይል ቆየ በመጨረሻው አመት የክለቡ ቆይታው በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ 19 ጎል በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ ለመሆን በቃ፡፡ ከአራት አመት በፊት ያለመውን የኮከብነት ማእረግ አገኘ በአመቱ አመርቂ እንቅስቃሴ ያደረገው ታፈሰ በኢትዮጵያ ቡና ተፈላጊ ሆነ ፡፡ እናም ቡናን ተቀላቀለ፡፡

ታፈሰ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚደግፈውና የሚመኘው አንድ ክለብ ነበር፡፡ መቼ ነው ለዚህ ክለብ የምጫወተው እያለ ሁሌም ያልማል ህልም  በ 1998 እውን ሆነ  በ 1998 ፍፃሜ የሚወደውን ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቀለ፡፡ በመጀመሪያ አመት የክለቡ ቆይታው ፍፃሜ በውዝግብ ነበር ያሳለፈው፡፡ በአመቱ ያስቆጠራቸው ጎሎች በትክክል ባለመመዝገባቸው የኮከብ ግብ አግቢነቱ ለርሱ ሲገባ ለበረከት አዲሱ መሰጠቱን ያምናል ሀረር ላይ ያስቆጠራቸው ጎል ስላልተመዘገበለት ለፌዴሬሽኑን መበደሉን ያምናል፡፡ ይሁንና የክለቡ ደጋፊዎች በግል የኢትዮጵያ ቡና አርማ ያለበትን ወርቅ ገዝተው ሸለመው ማበረታታቸውና አይዞህ ማለታቸው ከደረሰበት የሞራል ጉዳት እንዲያገግምና ወደ ብቃቱ እንዲመለስ እንዳስቻለው ያምናል፡፡ ቡና በ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ከፌዴሬሽኑ ጋር ባለመግባባት ለብቻቸው ውድድር ካዘጋጁት የክለቦች ህብረት አንዱ ስለነበር ውድድሩን ያደረገው በዚያው   በ 2000 ዓ/ም ታፈሰ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሳልሃዲን ሰኢድ እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ በኮከብ አግቢ ለመሆን የተፎካከሩበት  ነበር፡፡ በመጨረሻው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ላይ አራት ጎል ያስቆጠረው ሳልሃዲን የኮከብ አግቢነቱን ፍኩኩር በአሸናፊነት  አጠናቀቀ፡፡ ይሁንና ታፈሰ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ በመመረጡ በሌላ  ትልቅ ሽልማት ተካሰ፡፡ በቀጣዩ አመት 2001 በሌላ ስኬት ቀጠለ፡፡ 23 ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ አጠናቀቀ፡፡ በዮርዳኖስ አባይ የተያዘውን የምንግዜም የከፍተኛ ግብ አግቢነት ለመጋራት ሳይችል ቀረ፡፡ ዬርዳኖስ   በ 1993 ያስቆጠረው 24 ጎል ነበር፡፡  

ታፈሰ   በ 2002 ዓ/ም ከጉዳቱ ጋር እየታገለ ያሳለፈ ሲሆን በተለይ የመጀመሪያ ዙር ያልተሰለፈባቸው ጨዋታዎች በርካታ ናቸው፡፡ በሁለተኛው ዙር ከጉዳቱ አገግሞ መሰለፉን ተከትሎ ወደ ብቃቱ መመለስና በርካታ ጎሎችን ማስቆጠር ቻለ፡፡ በተለይ አዳማ ከነማን 6-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ አባት ጎል ማስቆጠሩ በአንድ ጊዜ ወደ ኮከብ ግብ አግቢነቱ ፉክክር የተመለሰበት ነበር፡፡


ታፈሰ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 

ታፈሰ ተስፋዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን ተመርጦ የተጫወተው የመብራት ሀይል ተጫዋች ሳለ  በ 1995 ዓ/ም ነው ለወጣት ብሔራዊ ቡድኑ በተመረጠበት ወቅት ነበር፡፡  በ 1997 ለዋናው ብሔራዊ ቡድኑ ለተመረጠበት ወቅት ነበር፡፡  በ 1997 ለዋናው ብሔራዊ ቡድን ተመረጠ፡፡ ከዚህ አመት ጀምሮ በተካሔዱ የኢትዮጵያ ቡድን ምርጫዎች ሁሉ የታፈሰ ስም ተካትቷል  በ 1997 እና 1998 የሴካፋ ሻምፒዮን በመሆንም የወርቅ ሜዳልያዎችን አጥልቋል፡፡   በ 2002 ኬንያ ላይ የተካሔደው የሴካፋ ውድድር ላይም ለሀገሩ ተጫውቷል፡፡

ቁጭት

ታፈሰ ኢትዮጵያ ቡናን ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያፈቅረውና ሁሌም በልቡ ውስጥ ያለ ክለብ መሆኑን ይናገራል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ከሌሎች ክለቦች ከየመን ክለቦች ሳይቀር የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝለት  የዝውውር ጥያቄ ቢቀርብለትም ለክለቡ ታማኝ በመሆን እስከ አሁን ቆይቷል፡፡ በቀጣይም ከዚህ ክለብ የተጫዋችነት ዘመኑ እንዲጠናቀቁ ይፈልጋል፡፡ ይሁንና ይህ የሚወደው ክለብ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዋንጫ አንስቶ አለማወቁ ሁሌም ይቆጨዋል፡፡ " ሲኖ  ጋሞ ናያ ታፌ " እያሉ የሚያዜሙለት የክለቡ ደጋፊዎችን ፍላጎት  ሣያረካ ኳስ ማቆም አይሻም፡፡ ይህን ቁጭቱን  በ 2003 የውድድር ዘመን እንደሚያወጣም ተስፋ ያደርጋል፡፡

ethiofootball.com


 
 
 
 
 
 
 
Goal Statistics
During the match Goal
Adama City Vs Dedebit 1
Adama City Vs Fasil City 1
Adama City Vs Commercial Bank 1
Fasil City Vs Adama City 2
Total 5
Adama City Players Goal Statistics
Tafesse Tesfaye 8
Suleman Mehamed 1
4
Mujib Kasim 4
Player? 2
Bulcha Shura 3
Surafel Dagnachew 3
Dawa Huttessa 2
Sisay Tola 1
Micharl George 2
Chakuri 1
 
 
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro