home
About Us
Player Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Adane Girma St.George
St.George

 
Name: Adane Girma  
Weight: 80  
Age: 00  
Height: 1.83  
Position: CS  
Club: St.George  
 
አዳነ ግርማ 

ስም:   አዳነ ግርማ 
የሚጫወትበት ክለብ: ቅዱሰ ጊዮርጊስ
የማልያ ቁጥር: 19

አዳነ ግርማ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጤታማ ከሆኑና ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች አንዱ ነው፡፡ የሚጫወተው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ተመራጭ ነው፡፡

የልጅነት  ዘመን 

አዳነ ግርማ የተወለደው በሞቃታማዋ የደቡብ መዲና ሀዋሳ ከተማ ነው፡፡ በተለምዶ ኮረም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መንደር ሲሆን በዚህ ሰፈር ኮረም ሜዳ ተብሎ የሚጠራ የእግር ኳስ ሜዳ መኖሩ በሀዋሳ ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ተጫዋቾች መገኛ ነው፡፡ ከአዳነ ግርማ በተጨማሪ ሙሉጌታ ምህረት፣ በሃይሉ ደመቀ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ዮናታን ከበደና ደረጃ ሀይሉን የመሳሰሉ ተጫዋቾች መገኛ ይኸው ኮረም ሜዳ ነው፡፡ እናም አዳነም ከህፃንነቱ ጀምሮ ለእግር ኳስ ቅርብ ሆኖ ነው ያደገው፡፡ በፍጥነትም የእግር ኳስ ክህሎቱ አደገ፡፡

ቀጭንና ደቂቃ የነበረው አዳነ የፊት አጥቂ በመሆን ነበር ከልጅነቱ ጀምሮ መጫወት የጀመረው በ  1992 በፕሮጀክት በመታቀፍ ስልጠና መከታተል የጀመረው አዳነ ከሌሎች ልጆች ጎልቶ የሚታይ ችሎታ ባለቤት መሆኑን አሳየ፡፡ በዚሁ አመት በደብረማርቆስ በተካሔደው የኢትዮጵያ የፕሮጀክቶች እግር ኳስ ውድድር ጎልተው ከታዩ ተጫዋቾች አንዱ በመሆን በብሔራዊ ደረጃ ተመረጠ፡፡ የተመረጡት ታዳጊዎች ወደ ስዊድን በማቅናት ዘመናዊ ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሎ ሀዋሳ ላይ እንዲቆዩ ተደረገ፡፡ ይሁንና የታቀደውን ባለመሳካቱ ወደየመጡበት እንዲመለሱ ተደረገ፡፡

አዳነና ሀዋሳ ከነማ 

አዳነ ግርማ አዶ በ 1994 በከተማዋ ብሎም በክልሉ ብቸኛ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የነበረውንና በከተማው ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ሀዋሳ ከነማን ተቀላቀለ፡፡ በፍጥነት ውጤታማ በመሆንም ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ለመካተት በቃ፡፡ በአጥቂነት የጀመረውንም ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ለመካተት በቃ፡፡ በአጥቂነት የጀመረው አዳነ ወደ ተከላካይ አማካይነት አንዳንዴም በተከላካይነት ተመልሶ እንዲጫወት ተደረገ፡፡ በሁሉም ቦታዎች ውጤታማ ሆነ፡፡

1996 ለሀዋሳ ከነማና አዳነ ግርማ ልዩ አመት ነበር፡፡ የክልል ክለቦች የዋንጫ ባለቤት አይደለም ተፎካካሪ እንኳን በማይሆኑበት ዘመን ሀዋሳ ከነማ ዋንጫውን በመውሰድ ታሪካዊ ክለብ ሆነ፡፡ ሙሉጌታ ምህረት፣ በኃይሉ ደመቀ፣ አዳነ ግርማደግ የቡድኑ ተጠቃሽ ሰዎች ነበሩ፡፡ በ 1997 ደግሞ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ባለቤት ሆነ፡፡

በ 1998 አዳነ የአዲስ አበባ ክለቦች ትኩረት አረፈበት፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ባንኮች አዳነን በማስፈረም የግሉ አደረገው፡፡ አስቀድሞ ለባንኮች የፈረመው አዳነ ከአሳዳጊ ክለቡ ሀዋሳ ከነማ የቀረበለትን አትሂድ የሚል ተማፅእኖ ለመቀበል ፍላጎት ቢኖረውም አንድ ጊዜ ለባንኮች ፈርሟልና ለሀዋሳ ከነማ ሌላ ኮንትራት መፈረም ለቅጣት ይዳርገው እንደሆን እንጂ የሚፈይድለት ነገር አልነበረም፡፡ እናም በሀዋሳ ለመቆየት ፍቃደኛ በመሆኑ ባንኮች ፊርማውን እንዲቀዱለት ሀዋሳዎች ጥረት ጀመሩ፡፡ ባንኮችም ተጫዋቹን ይፈልጉት ነበርና በቀላሉ እጅ መስጠት አልፈለጉም የአዳነ ግርማ ተፈላጊነት ጨመረ፡፡ ሀዋሳዎች ጉዳዩን የስፖርት ፍላጎት እንዳላቸው ለሚነገርላቸው ለወቅቱ የክልሉ ርእስ መስተዳደር ጉዳዩን አሰሙ፡፡ ርእሰ መስተዳደሩም ከባንኮች ክለብና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና በማግባባት አዳነ ሀዋሳ እንዲቆይ አደረጉ፡፡ ይህን ያደረጉት የወቅቱ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር የአሁኑ የፌደራል መንግስት ተጠሪ አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ ናቸው፡፡

በ 1998 እና 1999 ሀዋሳ ላይ ቆየ፡፡ በ 99 ከወቅቱ የፌዴሬሽኑ ፕሩዘዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋር ያልተስማሙት ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅ/ጊዮርጊስ፣ መብራት ሀይል፣ ባንኮች፣ መድህን እና ሌሎች በርካታ ክለቦች ከፕሪሚየር ሊጉ ራሳቸውን በማግለላቸው ሌሎች ክለቦች ተክተዋቸው የሊጉ ውድድር ቀጠለ፡፡ ሀዋሳ ከነማ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ አዳነም ይህ ድሉ የመጨረሻው ሆኖለት ካሳደገውና ለስምንት አመት አብሮት ከቆየው ክለብ ጋር ተለያየ ቅ/ጊዮርጊስን 80,000  ብር የዝውውር ገንዘብ ተቀላቀለ፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን በሀገሪቱ ከፍተኛው ነበር፡፡

አዳነ በቅዱስ ጊዮርገስ   

አዳነ ግርማ ከ &ampnbsp2000 ዓ/ም ጀምሮ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በሦስቱም ተከታታይ አመታት ቅ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ አደነ ሦስቱንም ዋንጫዎች አብሮ ስሟል፡፡

በዘንድሮው 2002 ውድድር የመጀመሪያ ዙር ቅ/ጊዮርጊስ ከተጎዱበት 10 ተጫዋቾች አንዱ ነበር፡፡ ለጉዳት ከመዳረጉ በፊት ግን ወደ ናይሮቢ ባቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመራጭ ነበርና ሀገሩን አገልግሏል፡፡ ከኢንተርናሽናል ውድድር መልስ ለክለቡ ጥቂት ጨዋታዎችን ካደረገ በኃላ ጉዳት አጋጠመው፡፡ የሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሩ በፊት ክለቡ በነበረበት የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድር ተጫውቷል፡፡ በሱዳን ኦምደርማን ስታድየም ከአልሜሪክ ጋር በተደረገው የመልስ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ 1 ለ 0  መምራት ችሎ ነበር ፡፡ ከፓትሪክ አችን የተሻገረለትን ኳስ ወደ ጎል በመለወጥ ክለቡን መሪ ያደረገው ደግሞ አዳነ ነበር፡፡ ይሁንና ቅ/ጊዮርጊስ መሪነቱን በማስነጠቁ 3 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውች ሆኗል፡፡

በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ አገግሞ የተሰለፈው አዳነ ለክለቡ ሻምፒዮንነት ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ በተለይ ወሳኝ ግቦችን በማስቆጠርና ቡድኑን ለድል በማብቃት ተጠቃሽ ሚና ተወጥቷል፡፡ ክለቡ አምስት ጨዋታዎችን እየቀሩት ሻምፒዮን መሆንን ሲያረጋግጥ አዳነ 13 ግቦችን በማስቆጠር የክለቡ ኮከበ ግብ አግቢ ነው፡፡ ከእነዚህ 13 ግቦች 9 ያስቆጠረው በሁለተኛው አጋማሽ ነው፡፡

በተለይ ደደቢትና ኢትዮጵያ ቡናን በመሳሰሉ ቡድኖችን ሲያሸንፍ የድል ግቦችን በማስቆጠር ወሳኝነቱን አስመስክሯል፡፡ ደደቢትን 2 ለ 0 ሲረቱ ሁለቱንም ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፉም ብቸኛዋን ጎል ያስቆጠረው አዳነ ግርማ ነው፡፡ አዳነ ያስቆጠራቸው ግቦች ከተሰለፈባቸው ጨዋታዎች አንፃር ሲሰላ ከፍተኛ ግብ አግቢ ነው፡፡ በ&ampampnbsp16 ጨዋታዎች 13 ግቦችን ከመረብ አገናኝቷል፡፡ 
አዳነ በብሔራዊ ቡድን 

አዳነ ግርማ በሐዋሳ ከነማ ታይቶ ውጤታማ ከሆነበት 1996 ጀምሮ የብሔራዊ ቡድኑ ተመራጭ ነው፡፡ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ አዳነን ያልመረጠ ባለሙያ የለም፡፡ ሁለቱን የሴካፋ ዋንጫዎች በ 1997 እና 1998 ካነሱ ተጨዋቾች ይጠቀሳል፡፡ በ 2002 ሀገሪቱ ከቅጣት መልስ በተሳተፈችበት የኬንያው የሴካፋ ውድድርም ተመራጭ ነበር፡፡
የአዳነ ልዩ ችሎታ- ሁለገብነት 

አዳነ እግር ኳስን ሲጀምር በአጥቂነት ይሁን እንጂ ያልተሰለፈበት የተጫዋችነት ቦታ የለም፡፡ አዳነ መሰለፍ ያልቻለው በግብ ጠባቂነት ስፍራ ብቻ ነው፡፡ አጥቂ፣ አማካይ፣ የመስመር ተመላላሽ /winger/ የመስመር ተከላካይ፣ መሃል ተከላካይ ሆኖ ተጫውቷል፡፡ ግን የጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሚሊቱን ሰርዲዮቪች ሚቾ በአጥቂ ስፍራ ላይ ነው እያጫወቱት ያሉት ጥሩ አጥቂ መሆኑንም በማሣየት ላይ ነው እያጫወቱት ያሉት ጥሩ አጥቂ መሆኑንም በማሣየት ላይ ነው፡፡
አዳነና ቅፅል ስሞች - አዶ፣ ወፍጮ

አዳነ ግርማ በሀዋሳ ከነማ ደጋፊና በአካባቢው የሚጠራው አዳነ ከሚለው  መደበኛ ሰሙ ይልቅ አዶ በሚለው ቅፅል ስሙ ነው፡፡ ሁሉም አዶ እያለ ይጠራዋል ይሁንና የተለየ ቅፅል ስምም ባለቤት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ወፍጮ  በሚለው ቅፅል ስሙ ይታወቃል፡፡ ይህን ስም ያወጡለት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ናቸው፡፡ አሰልጣኙ ሩዋንዳ ላይ በተካሄደው የ 1998 የሴካፋ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ይዘው ሻምፒዮን ሲሆኑ አዳነ ግርማ ሁሌም ቋሚ ተሰላፊ ውስጥ ያካትቱታል፡፡ ታዲያ አዳነን ተመራጭ ያደረገው የግል ክህሎቱ ብቻ አይደለም አካላዊ ብቃቱም ጭምር እንጂ፡፡ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ጎልቶ የሚታየውንና ስጋት ይፈጥራል ብለው የሚያስቡትን ተጫዋቸ እንዲያዝላቸው ብሎም ጎሸም እንዲያደርግላቸው የሚመርጡት አዳነ ግርማን ነው፡፡ እናም ሲመክሩት ና የኔ ወፍጮ በል ያን 9 ቁጥር ደህና አርገህ ፍጭልኝ ይሉታል  እሱም ይፈጫል ሌላ ጊዜም ና ወፍጮው  ይሉታል ይህች አጠራር የቡድን አጋሩ ደጉ አበበ ጆሮ ትደርሳለች ደጉም ለቡድኑ አባላት ይነግራል ሁሉም ዘንድ ትድርሳለች፡፡ እናም የአዳነ ቅፅል ስም ወፍጮ ሆኖ ይቀራል፡፡ ነገር ግን ወፍጮነቱን ከሌላ ነገር ጋር የሚያገናኙበት ተጫዋቾች አይጠፉም ለምግብ ሲቀርቡ በምግብ አይታማም የሚሉት አዳነ ደህና አድርጎ ይፈጫል ሲሉ ያሙታል፡፡   

ethiofootball.com

 
 
 
 
 
 
 
Goal Statistics
During the match Goal
St.George Vs Fasil City 1
A.A. City Vs St.George 1
St.George Vs Hawassa City 1
Electric Vs St.George 1
St.George Vs Arba Minch 1
Dedebit Vs St.George 1
St.George Vs Welayta Dicha 1
St.George Vs Diredawa City 1
Commercial Bank Vs St.George 1
Arba Minch Vs St.George 2
St.George Vs Defence Force 1
Welayta Dicha Vs St.George 1
Total 13
St.George Players Goal Statistics
Behailu Assefa 2
Ramkelo 3
Salahadine Said 14
Adane Girma 14
Alula Girma 1
Mentesenot Adane 5
Ayzak Ezendea 1
1
Abubeker Sani 5
Bruno Kone 1
Abdulkerim Nikema 1
 
 
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro