home
About Us
Player Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Ashenafi Girma Diredawa
Diredawa City

 
Name: Ashenafi Girma  
Weight: 59  
Age: 00  
Height: 1.73  
Position: MF  
Club: Diredawa City  
 
አሸናፊ ግርማ 

የሚጫወትበት ክለብ ፡  ድሬደዋ ከነማ 
የሚጫወትበት ስፍራ ፡  አ ማካይ 


አሸናፊ ግርማ በ 1990ዎች በኢትዮጵያ እግርኳስ ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ከሚነሱ ተጫዋቾች ይጠቀሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድሬደዋ ከነማን በአምበልነት እየመራ ይገኛል፡፡ 

የልጅነት ዘመን

አሸናፊ ግርማ የተወለደው በሞቃታማዋና የፍቅር ሀገር እየተባለች በምትቆላመጠው ድሬደዋ ከተማ ነው፡፡ በተለምዶ    ተብሎ በሚጠራው ሰፈር አካባቢ ሲሆን ጊዜው 1975 ዓ.ም ነበር፡፡ 

አሸናፊ ባደገበት ሰፈር ውስጥ በጨርቅ ኳስ የጀመረው የእግር ኳስ ሂወት በሀገሪቱ ተጠቃሽ ተጫዋች እስከመሆን አድርሶታል፡፡ ምንም እንኳን ከእድሜ እኩዬቹ አንፃር በአካል መጠኑ አነስ ያለ የነበረ ቢሆንም የእግር ኳስ ክህሎቱ ግን የተለየ ስለነበር ከሌሎቹ ጎልቶ ይታይ ነበር፡፡ ሳ.. ለተባለው የመንደሩ ክለብ እየተጫወተ እስከ 1990 ቆየ፡፡ በዚህ አመት የከተማዋ ክለብ የሆነው ድሬደዋ ጨርቃጨርቅ ዓይነት ውስጥ ገባ እናም የዚህ ክለብ አባል ሆነ፡፡ 

የክለብ ህይወት 

አሸናፊ በመጀመሪያው የትውልድ ከተማው ክለብ ድሬደዋ ከነማ ጋር አንድ አመት 1990 ነው፡፡ በቀጣይ አመት 1991 ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቀለ፡፡ ከመድን ጋርም የቆየውም በተመሳሳይ ለአንድ አመት ነው፡፡ በቀጣይ ዓመት ትልቅ ደረጃ የደረሰበትንና ታዋቂነትን ያተረፈበትን ኢትዮጵያን ቡናን ተቀላቀለ፡፡ 
በኢትዮጵያ ቡና አሰደሳች ጊዜን ያሳለፈው አሸናፊ ከቡናማዎቹ ጋር ሦስት ጊዜ የጥሎ ማለፍ ሁለት ጊዜ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን አስተስቷል፡፡ በ 1994 በአወዛጋቢ ሁኔታ የኢትዮጰየ ቡና የምንግዜም ተቀናቃኝ የሆነውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቀለ፡፡ ይሁንና በጊዮርጊስ የተረጋጋ ጊዜ ማሳለፍ አልቻለም፡፡ በቡና ደጋፊዎች ዘንድ ውግዘትን አስክትሎበታለ፡፡ መረጋጋት የተሳነው አሸናፊ ያስቀየማቸውን ደጋፊዎች ይቅርታ ጠይቆ ወደ ቡና ተመለሰ በቀጣዮ ዓመት 1995 ወደ ብቃቱና አስደሳች ጊዜው ተመለሰ፡፡ የዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎም ተመረጠ ቀጣይ ሁለት ዓመታትን በቡና አሳለፈ በ 1997 ዓ.ም ወደ የመን በመጓዝ የፕሮፌሽናልነት ህይወትን አይቷል፡፡ 

አሸናፊ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገሩ ውጭ የተሰለፈበት ክለብ በየመን ዋና ከተማ ሰንአ የሚገኘው አህሉ ሰንአ ነው፡፡ በዚህ ክለብ ሁለት ዓመት ካሳለፈ በኃላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ከመብራት ሀይል ጋር 1999 የውድድር ዘመንን አሳልፏል፡ በ 2000 ዓ.ም ዳግም ወደ የመን በማቅናት ሸባብ ሀድራሞት ለተባለው ክለብ ለመሰለፍ ችሏል የአንድ አመት የየመን ቆይታውን ካጠናቀቀ በኃላ ወደ ትውልድ ከተማው ተመልሶ ተጫወተ፡፡ 

በ 2001 ድሬደዋ ከነማ ፕሪሚየርሊጉን መቀለቀሉ አሸናፊ ከ 10 አመት በኋላ ለትውልድ ከተማው ክለብ ዳግሞ እንዲሰለፍ አስቻለው፡፡ በዚህ አመት በአብዛኛው አዳዲስ ተጫዋቾችን የያዘው ድሬደዋ በፕሪሚየርሊጉ ለመቆየት ፈተና ሆኖበት ነበር፡፡ በሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ለዚህ ማሳያ ሆኗል፡፡ በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ አራት ጨዋታዎችን በሜዳው ድሬደዋ ስታድየም ያደረገው ድሬደዋ ከነማ አራቱንም ድል በማድረግ አንሰራራ በቀሪዎቹ ጨዋታዎችም ውጤታማ በመሆን በአመቱ መጨረሻ ያለስጋት በሊጉ መቆየቱን አረጋገጠ፡፡ ለዚህ ውጤታማነቱ የአምበሉ አሸናፊ ግርማ አሰተዋጽኦ የጎላ ነበር፡፡ 
በአዲሱ የውድድር ዘመን 2002 አሸናፊና ድሬደዋ ዳግሞ ተለያዩ፡፡ ከአዲስ መጭው ሜታአቦ ቢራ ፈርጠም ያለ የዝውውር ሂሳብ የቀረበለተ አሸናፊ ድሬደዋን ለቆ የሠበታውን ክለብ ሜታን ተቀላቀለ፡፡ በዝውውሩ የተቀበለው 120,000 ብር ነው፡፡ ይሁንና የአሸናፊ ልብ ዳግም ወደ ቡና መመለስ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተሳካለትም፡፡ በመጀመሪያው ዙር ሜታ አቦ ቢራ የመጨረሻ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ አሸናፊ ቅጣትና ጉዳት በብዙ ጨዋታዎች ላይ እንዳይሰለፍ አግዶታል፡፡ ለውድድር አመቱ አጋማሽ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ሜታ የከፈለውን ገንዘብ በመመለስ ወደ ድሬደዋ ከነማ ተመልሷል በሊጉ ለመቆየት እያደረገ ያለውንም ጥረት እያገዘ ይገኛል፡፡ 

የብሔራዊ ቡድን

አሸናፊ ግርማ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመሰለፍ ግልጋሎቱን አበርክቷል፡፡ አሹ ለመጀመሪያ ጊዜ አረንጓዴውን የሀገሩን ማሊያ የለበሰው በ 1991 ለኢትዮጵያ መድን እየተጫወተ ሳለ ነበር፡፡ ሞዛምቢክ ላይ በተካሄደው የአፍሪካ ታዳጊ ቡድን ላይ በተሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ላይ ተመርጦ ተጫውቷል፡፡ ቡድኑ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ አሸናፊም የመሀል ክፍሉን በመምራት የድርሻውን ተወጥቷል፡፡ 

በ 1992 ለወጣት ቡድን /ከ 20 አመት በታች/ ተመርጦ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ በተካሄደው የሴካፋ ሻምፒዮና ላይ በመሳተፍ ሦስተኛ ደረጃን ያገኘው ቡድን ላይም የአሸናፊ የአማካሪነት ሚና እንደተጠበቀ ነበር፡፡ 

በ 1993 የተካሔደው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ስታስተናግድ ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዙያቶ ውጤታማ የሆነ ቡድን ገንብተው ነበር፡፡ የአሁኑ የአፍሪካ ሻምፒየናው ክለብ ቲፒ ማዛምቤ አሰልጣኝ የሆኑት ጋርዚያቶ የመሩት ቡድን አራተኛ ደረጃን በማግኘት ለአለም የወጣቶች ሻምፒዮና ሲያልፍ አሸናፊ ግርማ የቡድናቸው መሠረት ኳስ እንሸራሻሪ Play maker ተጫዎች ነበር፡፡
 
በዚሁ ዓመት ቢድኑ በወጣቶች የአለም ዋንጫ ለመሳተፍ ወደ አርጀንቲና ሲያቀና አሸናፊ የአማካይ ክፍሉ ቀዳሚ ተመራጭ መሆኑ ቀጥሏል፡፡ በአርጀንቲናው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ  ዙር ማለፍ ባትችልም አድናቆት የተቸረው እንቅስቃሴ ስታሳይ የአለምን ትኩረት የሳበ ቀዳሚ ኢትዮጵያ ተጫዋች አሸናፊ ግርማ ነበር፡፡ በቀጣይ ወደ አውሮፖ የመሄድና ፕሮፌሽናል ተጫዋች ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ 

በ 1994፣ 97 እና 98 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የኬካፋ ሻምፒዮን ሲሆን አሸናፊ ግርማ የቡድኑ ተመራጭና ተሰላፊ ለመሆን ሦስት ጊዜ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሻምፒዮንነትን ክብር አግኝቷል፡፡ በ 94 እና 97 አዲስ አበባ ላይ ሻምፒዮን የሆነው የአስራት ሀይሌ በ 98 ደግሞ ሩዋንዳ ላይ ሻምፒዮን በሆነው የሰውነት ቢሻው ቡድን ውስጥ ነበር የተካተተው፡፡


አሸናፊና የተለየው ባህሪው  
አሸናፊ የዝናና ስኬቱን ያህል አወዛጋቢ የሚባሉ ጊዜያትን አሳልፏል፡፡ በተለይ በ 1994 ወደ ጊዮርጊስ በተዛወረበት ወቅት በብዙሃኑ የቡና ደጋፊዎች ጋር የገባው ውዝግብ ቀዳሚ ነው፡፡ በችሎታው አብዝቶ መተማመኑና ከተጫዋቾች ከአሰልጣኞች የክለብ ኃላፊዎችና ዳኞች ጋር በተደጋጋሚ ለግጭት እንደሚዳርገው ይነገራል፡፡ 

የማይነጥፈው የአሸናፊ ብቃት 

አሸናፊ ግርማ ለበርካታ አመታት በተጫዋችነት ዘልቀው አሁንም ሜዳ ውስጥ ከሚታዩ ተጫዋቾች ይመደባል፡፡ አሹ በተጫወተባቸው ክለቦች ሁሉ የተመልካች አይንን የሚስቡ ማራኪና ውጤታማ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ይታወቃል፡፡ ደካማ ለሚባሉ ቡድኖች ተሰልፎ እየተጫወተ እንኳን ውጤታማ መሆን ተችሎታል፡፡ ክለቡ ሲሸነፍ ለእይታ መብቃቱ አይቀሬ ነው፡፡ በተቃራኒ ሜዳ ክለቡ ሲያሸንፍ የተሸናፊው ክለብ ደጋፊዎች ሳይቀሩ ከመቀመጣቸው  ተነስተው ለአሸናፊ ያጨበጨቡበት ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ እናም አሸናፊ የተጫዋችነት የቆይታ ዘመን ሳይገድበው በሜዳ ውሰጥ ብቃቱን እያሳየ ያለ ተጫዋች ነው፡፡ 

ethiofootball.com

 
 
 
 
 
 
 
---
---
 
 
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro