home
About Us
Player Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Andualem Negussie Woldya
Woldya City

 
Name: Andualem Negussie  
Weight: 70  
Age: 00  
Height: 1.75  
Position: CS  
Club: Woldya City  
 
አንዷለም ንጉሴ አቤጋ

ስም ፡ አንዷለም ንጉሴ
የሚጫወትበት ክለብ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቀድሞ የነበረበት ክለብ: ሰበታ ከነማ 
የሚጫወትበት ስፍራ ፡ አጥቂ 
የማልያ ቁጥር ፡

አንዷለም ንጉሴ የሰበታ ከነማ ተጫዋች ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ጊዮርጊስና ለሙገር ሲምንቶ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በተደጋጋሚ የመጠራት እድል አግኝቷል፡፡

የልጅነት ዘመን 

አንዷለም ንጉሴ የተወለደው በ 1975 ዓ/ም በአሰላ ከተማ ነው፡፡ ሀገራችንን በአለም አደባባይ ሠንደቅ አላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አትሌቶች መገኛ የሆነችው አሰላ ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በአሰላ ነፋሻማ ሜዳዎች ይጫወት የነበረው አቤጋ የእግር ኳስ ክህሎት በወቅቱ አዲስ የተዘረጋው እግር ኳስ ፕሮጀክት መልማዮች ትኩረት እንዲስብ አደረገው፡፡

በ 1993 ዓ/ም ደግሞ በአምቦ፣ ድሬደዋና አዳማ ሁለተኛ ቡድኖች የነበሩት ሙገር ሲሚንቶ መልማዮች አይን ውስጥ ገባ፡፡ እናም ለሙገር ሁለተኛ ቡድን /B/ ተመረጠ፡፡ አዳማ ላይ ሆኖም ስልጠናውን ተከታተለ፡፡

የሙገሩ አቤጋ 

አንዷአለም በአዳማው የሙገር ተጠባባቂ ቡድን የተጫወተው ለአንድ አመት 1993 ዓ/ም ብቻ ነው፡፡ በቀጣይ አመት 1994 ዋናው ቡድንን በመቀላቀል ጥሩ እንቅስቃሴ አደረገ፡፡ ሶስት አመት የሙገር ቆይታውም ውጤታማ በመሆኑ በሀገሪቱ ጥሩ የሚጫወቱ ተጨዋቾችን በማስፈረም ወደ ሚታወቀው ቅዱስ ጊዮርጉስ ተዛወረ፡፡

የጊዮርጊሱ አቤጋ 

አንዷለም ንጉሴ ውጤታማ  ዘመን ያሳለፈው ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ነው፡፡ ክለቡን በተቀላቀለበት የመጀመረያ አመት 1996 ዋጋ ማግኘት አልተሳካለትም፡፡ በተደጋጋሚ ሻምፒዮን ይሆን የነበረው ቅ/ጊዮርጊስ ከዋንጫው ፉክክር ውጭ በመሆኑ ሻምፒዮንነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ክልል ወጣ፡፡ ሀዋሳ ከነማ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ �-2001 ከተካሄዱት አምስት የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመናት በአራቱ ቅ/ጊዮርጊስን ሻምፒዮን ሲሆን የአቤጋ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበር፡፡

በቅ/ጊዮርጊስ ከጓደኞቹ ሙሉአለም ረጋሳና ዳዊት መብራቱ ጋር በመሆን ውጤታማ ከመሆን ባሻገር ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መሆን ችለው ነበር፡፡ ይሁንና......አሰልጣኝ ሚቾ ጋር በስተመጨረሻው እንዳልተስማሙ የተነገረ ሲሆን ይህ አለመስማማታቸውም ክለቡን በመልቀቅ ሶስቱም ሰበታ ከነማን እንዲቀላቀሉ እንዳደረጋቸው ይሰማል፡፡

የሰበታው አቤጋ

በ 2002 የውድድር ዘመን በርካታ ተጫዋቾችን በማዛወር ተጠናክሮ የቀረበው ሰበታ ከነማ የዋንጫ ተፎካካሪ ይሆናል የሚል ግምም ተሰጥቶት ነበር፡፡ አንዷለም አሁንም ከሰበታ ጋር ሆኖ እያሳየ ያለው ብቃት ችሎታው እንዳልነጠፈ የሚያሳይ ነው፡፡ በዓመቱ የፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ሰበታ ከቅ/ጊዮርጊስ የተገናኘ ሲሆን አቤጋም የቀድሞ ክለቡን የማያስቆም እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ በጭንቅላት በመግጨት ያስቆጠራት ግብ በእለቱ ዳኛ ሳትፀድቅ መቅረቷም አወዛጋቢ ሆና ነበር ያለፈችው፡፡ አቤጋ አሁንም ቢሆን በአካላዊ ብቃቱና በክህሎቱ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሁን የክለቡ አሰልጣኝ አብረሃም ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ይዘው ወደ ናይሮቢ በተጓዙበት ወቅት አቤጋ ቀዳሚ ምርጫቸው ነበር፡፡ 

ብሔራዊ ቡድን 

አንዷለም ንጉሴ በቅዱስ ጊዮርጊስ ውጤታማ ዘመን ሲያሳልፍ በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመመረጥ እድል አግኝቷል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በ 1997 እና 1998 አዲስ አበባ እና ሩዋንዳ ላይ ሻምፒዮን ሲሆን አቤጋ የአስራት ሃይሌም ሰውነት ቢሻውም ተመራጭ ነበር፡፡ ሁለቱንም ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥልቋል፡፡ ኢትዮጵያ ፊፋ ከጣለባት እገዳ መነሳት በኃላ ወደ ኢንተርናሽናል ውድድር ስትመለስ አቤጋም ደግሞ ሀገሩን ለማገልገል አረንጓዴውን ማልያ አጠለቀ፡፡ ናይሮቢ ላይ በተደረገው 33ኛው የሴካፋ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ በተጋባዡ ታንዛንያ 1 ስትሸነፍ ከውድድር የመውጣት እድሏ ሰፋ፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ጅቡቲን 5 ለ 0 የረታው ቡድኑ በዚህ ጨዋታ አቻ ቢወጣ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ያረጋግጥ ነበር፡፡ ቡድኑ አቻ የሚሆንበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይሁንና የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት አንዷለም ንጉሴ ቢመታም ጎል ማድረግ ባለመቻሉ ቡድኑ ከውድድሩ ውጭ ለመሆን ተገደደ፡፡ አቤጋም ከሚያስቆጩት ጨዋታዎች አንዱ መሆኑን ያወሳል፡፡


 
 
 
 
 
 
 
Goal Statistics
During the match Goal
Jimma abbabuna Vs Woldya City 1
Woldya City Vs Electric 1
Woldya City Vs Adama City 1
Total 3
Woldya City Players Goal Statistics
Chala Driba 2
Habtamu Shewalem 1
Andualem Negussie 3
Adamo mohammed 1
3
 
 
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro