home
About Us
Players Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Ethiopian Coffee
 
  PROFILE
ኢትዮጵያ ቡና  

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ 

Website:http://ethiopianc offeesportclub.com
የተመሰረተበት ዘመን፡ 1975 ዓ/ም 
የክለቡ የቅቱ አሰልጣኝ፡ድራገን ፓፓዲች
ም/አሰልጣኝ ፡-  እድሉ ደረጄ
የበረኛ አሰልጣኝ :- ውብሸት ደሳለኝ
የህክምና ባለሙያ ፡- ይስሃቅ ሽፈራው  
የቡድን መሪ ፡- አብዱ ሳላህ/ፈቱሼ/ 
የክለቡ የወቅቱ አምበል፡ 

ክለቡ ያገኛቸው ክብሮች: - የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፕዮን -1-2003 ዓ.ም።

- የኢትዮጵያ ሻምፒዮና - 1 - 1989
- የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና -4- 1989፣ 1992፣ 2000
- የኢትዮጵያ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ - 3- 1989፣ 1992፣ 2000 
- የክለቦች ህብረት - 1999

Ethiopian Coffee Players on the pitch


ኢትዮጵያ ቡና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ከሚነሱ ክለቦች አንዱ ነው፡፡ ክለቡ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17 አመት ቆይታ ከአንድ ጊዜ በላይ  ዋንጫ  ማንሳት  የልታደለ ቢሆንም  የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት በመሆን ቀዳሚ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሻምፒዮን በጥሎ ማለፉና አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫም ድል አግኝቷል፡፡

ምስረታ''''

ኢትዮጵያ ቡና የተመሰረተው በ1975 ዓ/ም በቡና ቦርድ ስረ ነበር።ስያሜውም ቡና ገበያ ስፖርት ክለብ የሚል ነበር። በቀጣይነት የቡና ላኪዎች ማህበር ከምርት ገበያ ጋር በመሆን በጀት እየመደቡለት በቦርድ በመመራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ''''

የኢትዮጵያ ሻምፒዮን''''

ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጰያ ሻምፒዮና የተካሄደበት የመጨረሻው አመት 1989 ዓ/ም ሻምፒዮን በመሆን በስተመጨረሻው ድልን አጣጥሟል፡፡ በዚህ አመት ክለቡ ጠንካራ ደረጃ መድረስ የቻለበት ነበር፡፡ አሻረኝ ያለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ''''

ኢትዮጵያ ቡና የታሪኩ፣ የገናናቱን በርካታ ደጋፊዎች ባለቤት የመሆኑን ያህል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ከአንድ  ጊዜ በላይ  አለማንሳቱ ብዙዎችን የሚያስገርም ጉዳይ ነው፡፡ በአብዛኛው ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በማግኘት ነው የሚያጠናቅቀው፡፡ በ1996 ሀዋሳ ከነማ በመጨረሻው ጨዋታ በማሸነፍ ሁለተኛ የወጣበት ውጤት እስከመጨረሻው ጨዋታ የዋንጫ ተስፋን የሰነቀበት ነበር፡፡ ቡና በአብዛኛው የመጀመሪያ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ በተከታታይ በመጣል ችግር ውስጥ እየገባ በሁለተኛው ዙር መሻሻል እያሳየ መጓዙ ለውጤት ማጣቱ እንደምክንያት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ይህ ውጤት ማጣቱ የደጋፊዎችን ቁጥር አልቀነሰበትም እንዲያውም በተቃራኒው የቡና ደጋፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቀጥሏል፡፡''''

ቡና በአፍሪካ መድረክ

ኢትዮጵያ ቡና በአራት የአፍሪካ ውድድሮች የመሳተፍ እድል አግኝቷል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ በ1985 የኢትየጵያ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በ1990 ተሳትፏል፡፡ በዚህ እስከ አሁንም ብቸኛ ሆኖ በተመዘገበለት ተሳትፎው እስከ ሁለተኛ ዙር ለመዝለቅ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታው ሴይንት ማይክል ዩናይትድ ጋር ነበር የተገናኘው፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ በተቀናቃኙ ሜዳ 1ለ0 ተሸንፎ መመለሱ የማለፍ እድሉ ስጋት ውስጥ ቢገባም በመልሱ ጨዋተ በፍፁም የበላይነት 8ለ1 በማሸነፍ አለፈ፡፡ በዚህ ጨዋታ በወቅቱ የሀገሪቱ ምርጥ ተጫዋች እንደሆነ ይነገርለት የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ብቻውን አምስት ኃይሎችን በማስቆጠር አስገራሚ ብቃት አሳይቷል፡፡ በቀጣዩ የአንደኛ ዙር ማጣሪየ ከግብፁ አልአህሊ ጋር ተገናኘ፡፡ አል-አህሊ በአፍሪካ ስመገናና የሆነና የክፍለ ዘመኑ የአፍሪካ ምርጥ ክለብ ተብሎ የተመረጠ መሆኑ የቡና እጣ ፈንታ ከአል-አሃሊ አያልፍም ተብሎ ነበር፡፡ በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ጨዋታ አንድ አቻ በመልሱ በካየሮ ኢንተናሽናል ስታድየም በተካሄደው ጨዋታ ደግሞ ሁለት አቻ ተለያዩ፡፡ ከሜዳው ውጭ ሁለት አቻ የተለያየው ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳ ውጭ የተሻለ ጎል በማስቆጠሩ ወደ ሁለተኛው ዙር አለፈ፡፡ በሁለተኛው ዙር ከታንዛንያው ያንግ አፍሪካንስ ጋርተገናኘ፡፡ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ሁለት አቻ የተለያየው ቡና በመልሱ ጨዋታ ከሜዳው ውል 6ለ1 በመሸነፍ 8ለ3 በሆነ ድምር ውጤት ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ዓመት ያስመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያ ክለቦች ለመጨረሻ ጊዜ ያስመዘገቡት የተሻለ ውጤት ለመሆን በቅቷል ባለፋት 12 ዓመታት የተሳተፋት ቅ/ጊዮርጊስ፣ መብራት ሀይልና ሀዋሳ ከነማ ከአንደኛው ዙር በላይ ማለፍ አለቻሉም፡፡''''

ቡናና ደጋፊው ''''

የኢትዮጵያ ቡና በቀዳሚነት የሚጠራው ለስታድየም ውበትና ድምቀት ትልቅ አስተዋጽኦ በሚያበረክቱት ደጋፊዎቹ ነው፡፡ ክለቡ በኢትዮጰያ ፕሪሚየርሊግ ዋንጫ ማንሳት ባይችልም ከጊዜ ወደ ጊዜ የክለቡ ደጋፊዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል የክለቡ ደጋፊዎች በህብረት ተሰድረው ቆመው ተቃቅፈው እያዜሙ ሲንቀሳቀሱ ሲወዛወዙ ከሩቅ ለሚመለከት ቡናማ ወንዝ ላይ ማዕበል የሚንከባለል ነው የሚመስለው፡፡ በአዲስ አበባ ስታድየም ቀኝ ጥላ ፎቅ፣ ከታንጋ እና ሚስማርተራ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ግዛቶች ናቸው፡፡ የቡድኑ በጥሎ ማለፍና አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ስኬታማ ቢሆንም የሊጉን ዋንጫ አለማንሳቱ የሚቆጫቸው ደጋፊዎች ግን ጥቂት አይደሉም፡፡ የሊግ ዋንጫ ጥማችን አንድ ቀን ይሳካል እያሉ ተስፋ ሳይቆርጡ ክለቡን በመደገፍ ጉዟቸውን ግን ቀጥለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና ዋንጫ በተደጋጋሚ እንደማንሳቱ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ተደጋጋሚ ተሳትፎ አግኝትል፡፡ በተለይ ከ1991-93 በተከታታይ ለሦስት አመታት ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈ ክለብ ነው፡፡ ውድድሩ ያኔ የአፍሪካ የዋንጫ አሸናፊዎች ዋንጫ CAF cup winners cup ተብሎ ነበር የሚጠራው፡፡ በ1991 የብሩንዲው ኢንተርስታር ራሱን በማግለሉ ቅድመ ማጣሪያውን ካለፈ በኋላ በመጀመሪያው ዙር ለቀጣይ አመት 1992 የማላዊውን ቴልኮም ዎንደደርሰን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ካለፈ በኁላ በግብፅ ዛማሊክ ጋር ሦስት ላቻ ከተለያየ በኋላ በመለያ ምት ተሸንፎ ወጥቷል፡፡ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ በቀረበበት 1983 ከሁለተኛ ዙር አላለፈም የሞዛምቢኩ ማጂጄ ራሱን ካገለለበት በኋላ በካሜሩኑ ኩምስ ስትራይከርስ ተሸንፏል፡፡ ቡና በከፍ ካራም ሁለት ጊዝ ተሳትፋል፡፡ በ1986 በሱዳን አልምሩዳ በ1996 ደግሞ በሊቢያው አልናስር ተሸንፎ ከአንደኛው ዙር አላለፈም፡፡ ''''

ethiofootball.com
 
 
 
 
 
EthioPL Table
RankClub Name PGDPTS
1Dedebit2727
2Commercial Bank27-226
3Hawassa City2626
4Sidama Coffee2626
5A.A. City2626
6Welayta Dicha2626
7Diredawa City2626
8Fasil City2626
9Adama City2626
10St.George2626
11Ethiopian Coffee2626
12Arba Minch2626
13Defence Force2525
14Electric2525
15Jimma abbabuna123
16Woldya City11
Ethiopian Coffee Players:
Ethiopian Coffee Fixture :
Ethiopian Coffee Results:
HomeTeamScoreAwayTeam
Ethiopian Coffee0 - 0Commercial Bank
Defence Force0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Adama City
Electric0 - 0Ethiopian Coffee
St.George0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Dedebit
Arba Minch0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0A.A. City
Hawassa City0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Sidama Coffee
Diredawa City0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Fasil City
Welayta Dicha0 - 0Ethiopian Coffee
Commercial Bank0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Defence Force
Adama City0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Electric
St.George0 - 0Ethiopian Coffee
Dedebit0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Arba Minch
A.A. City0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Hawassa City
Sidama Coffee0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Diredawa City
Fasil City0 - 0Ethiopian Coffee
Ethiopian Coffee0 - 0Welayta Dicha
Ethiopian Coffee Players Goal Statistics x
Yabun William 9
Sadiq Sheto 5
3
Amanuel Yohanse 3
Gatosh Panom 3
Abdulkerim Mehamed 2
Elias Mamo 1
Fever Ekoy 1
Patrik 1
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro