home
About Us
Players Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Hawassa City
 
  PROFILE
ሀዋሳ ከነማ 

ሙሉ ስም ፡ ሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ 
ባለቤት ፡ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር 
ስታዲየም ፡ ሀዋሳ ስታዲየም 
 የወቅቱ  ዋና አሰልጣኝ ፡- ታረቀኝ አሰፋ 
ም/አሰልጣኝ ፡- በፍቃዱ ዘርይሁን 
የህክምና ባለሙያ ፡- መስፍን ላንጋኖ
 የበረኛ አሰልጣኝ፡- አምጣቸው ሃይሌ  
የወቅቱ አምበል ፡  
የቡድን መሪ ፡- ኡቴሳ ኡጋሞ 

ክለቡ ያገኛቸው ክብሮች:
- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ - 1996-1999
- የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮና - 1997 


ሀዋሳ ከነማ የደቡብ ክልል መዲና የሆነችውን ሀዋሳ ከተማን የሚወክል የእግር ኳስ ክለብ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ከአዲስ አበባ ክለቦች ውጭ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ብቸኛ ክለብ ነው፡፡

ምስረታ 

ሀዋሳ ከነማ የተመሰረተው በ 1970 ዓ/ም ነው፡፡ በወቅቱ የሲዳማ ክፍለ ሀገር ሻምፒዬና ተብሎ ይጠራ በነበረው የግዛቱ ውድድር ይሳተፉ ነበር፡፡

ሀዋሳ ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመርያው አመት 1990 ጀምሮ እየተሳተፈ ይገኛል። በመጀመርያዎቹ ስድስት አመታት እስከ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን ጥረት አድርጓል።


የስኬት አመታት 1996 እና 1999 

የሀዋሳ ከነማ ቀዳሚ ውጤታማ ዘመን ተብሎ የሚጠቀሰው 1996 ዓ/ም ነው ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ኒያላን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ ሀዋሳ በወቅቱ ያስመዘገበው ውጤት የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጭ እንዲሄድ ያስገደደ ነበር፡፡ በወቅቱ አሰልጣኝ ከማል አህመድ ኮከብ አሰልጣኝ ፤አምበሉ ሙሉጌታ ምህረት ደግሞ ኮከብ ተጫዋች ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በቀጣይ በ 1999 ዳግም ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ ይሁንና በዚህ አመት ሠባት የአዲስ አበባ ክለቦችን ጨምሮ ከውድድሩ ራሳቸውን በማገልገል ለብቻችው የክለቦች ህብረት ውድድር በሚል አዘጋጅተው ተወዳድረዋል፡፡ ሀዋሳ በውድድሩ የቀጠለ ሲሆን ከቀሩት ክለቦች የተሻለ ነጥብ በመሰብሰቡ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡ ሀዋሳ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተጨማሪ በ 1997 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ክለብ ነው፡፡

ሀዋሳ በኢንተርናሽናል ውድድሮች  

ሀዋሳ ከነማ ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ክለብ በመሆኑ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድል አግኝቷል፡፡ ይህም በ 1997 እና 2000 ዓ/ም ነው፡፡  በ 1997 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሳተፉ ከቅድመ ማጣሪያው ጨዋታ ከሱዳኑ አልሂላል ኦምደርማን ጋር ነበር የተደለደለው በመጀመሪያው ጨዋታ ካርቱን ላይ 2 ለ 1 ከተሸነፈ በኃላ በመልሱ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ አንድ አቻ በመለያየቱ 3ለ1 በሆነ ውጤት ተበልጦ ወደ አንደኛው ዙር ሳይልፍ ቀርቷል፡፡ በ 2000 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ሲሳተፍም የተደለደለው ከታንዛኒያው ሲምባ ጋር ነበር፡፡ ዳሬ ሰላም ላይ 3ለ0 ተሸንፎ በመመለስ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ አንድ አቻ በመለያየት በ 4  ለ 1 ጠቅላላ ውጤት ከውድድር ውጪ ሆኗል፡፡ በዚህም ሀዋሳ ከነማ ሁለት ጊዜ በተሳተፈበት የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር በቅድመ ማጣሪያ ደረጃ በመሰናበት ደካማ ውጤት ነው ያስመዘገበው፡፡
ሀዋሳ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫም በ 1998 ተሳትፏል ከሩዋንዳው ራዮንስፖርት ጋር የተገናኘው ክለቡ በመጀመሪያው ጨዋታ ኪጋሊ ላይ 1 ለ 0 ሲሸነፍ በመልሱ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ 1 ለ 0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት በመሸነፉ ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ቀደም ሲል ይካሄድ በነበረውና አሁን በተቋረጠው ካፍ ካፕ ተሳትፏል፡፡ ይህ ውድድር በየሀገሮቻቸው ላይ ሁለተኛ የወጡ ክለቦች የሳተፉበት የነበረ ነው፡፡ ሀዋሳ ከነማም በ 1991 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቶ በ 1992 በዚህ ውድድር ተሳትፏል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከሩዋንዳው ሙኩራ ቪክትሪ ጋር ነበር የተገናኘው አዲስ አበባ ላይ 2  ለ0 ማሸነፉ ኪጋሊ ላይ 1 ለ 0 ቢሸነፍም እንዲያልፍ አስችሎታል፡፡ በሁለተኛው ዙር በናይጄርያው ኢዋንያንው ናሽናል 3 ለ 2 በሆነ አጠቃላይ ውጤት በመሸነፉ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ 

 
 
 
 
 
EthioPL Table
RankClub Name PGDPTS
1St.George91222
2Adama City9720
3Dedebit9115
4Sidama Coffee9-114
5Diredawa City9013
6Defence Force9312
7Commercial Bank9011
8Electric9-111
9Ethiopian Coffee9-111
10Dashen Beer9-310
11Welayta Dicha9-710
12Arba Minch9-29
13Hawassa City9-59
14Hadiya Hosaena9-35
Hawassa City Players:
Hawassa City Fixture :
Hawassa City Results:
HomeTeamScoreAwayTeam
Hawassa City1 - 1Sidama Coffee
Diredawa City1 - 1Hawassa City
Hawassa City4 - 3Hadiya Hosaena
Welayta Dicha1 - 0Hawassa City
Hawassa City0 - 0Commercial Bank
Defence Force3 - 0Hawassa City
Hawassa City0 - 2Adama City
Electric2 - 1Hawassa City
Hawassa City1 - 0Ethiopian Coffee
Hawassa City Players Goal Statistics x
Gadisa Mebrat 2
Bereket Yitsak 2
1
Firdawok Sisay 1
Tafesse Solomon 1
Amele Michias 1
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro