home
About Us
Players Profile
Team Profile
Feedback
FAQs
 
 
 
Electric
 
  PROFILE
መብራት ሀይል 

ሙሉ ስም ፡ የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ስፖርት ክለብ 
የምስረታ ጊዜ ፡ 1953 ዓ/ም 
የወቅቱ አሰልጣኝ ፡ ብርሃኑ ባዬ
ም/አሰልጣኝ ፡ ኤርሚያስ ታፈረ
የበረኛ አሰልጣኝ :- ቅጣው ሙሉ
አምበል ፡ አዲሱ ነጋሽ 
የህክምና ባለሙያ - ጌታቸው ኃ/መስቀል
ክብሮች: - የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን - 1985, 1990, 1993

መብራት ሀይል ተብሎ በአጭሩ የሚጠራው የእግር ኳስ ክለብ በ 1953 ዓ/ም የተመሰረተና በቀጣዩ አመት 2003 ዓ/ም 50ኛ አመቱን የሚያከብር አንጋፋ ክለብ ነው፡፡ ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤታማ ሆኖ ቢቆይም በቅርብ አመታት ግል ከሊጉ ላለመውረድ የሚታገል ክለብ ሆኗል፡፡

ምስረታ 

የአሁኑ የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1953 የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ክለብ በሚል በ 1953 ዓ/ም ነው ለክለቡ በጀት የሚመድብለትና በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ባለስልጣን ነው፡፡ ክለቡ በርካታ ወጣት ተጫዋቾችን በመመልመልና ለትልቅ ውጤታ ለማብቃት ይታወቃል፡፡ ኤልያስ ጁሀር፣ ዮርዳኖስ አባይ፣ ታፈሰ ተስፋዬ ከዚህ ክለብ የተገኙ መሆናቸው ለዚህ ማሳያ ይሆናል፡፡ 
ክለቡ ከተመሰረተ ረዥም ጊዜ ቢያስቆጥርም ለመጀመሪያ ዋንጫ ለማግኘት የበቃው በ 1985 ዓ/ም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን ታሪካዊ ድል አስመዘገበ፡፡ የወቅቱ የቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩት ወንድማገኝ ከበደ ናቸው በዚህ አመት የጥሎ ማለፉንም ዋንጫ በመውሰድ የጣምራ ድል Double winner ባለቤት ሆኖ ነበር፡፡


አይረሴ ዘመናት 1990 እና 1993 

መብራት ሀይል የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተብሎ ይጠራ የነበረው ውድድር ወደ ሊግ ፎርማት ተቀይሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚል ስያሜ አግኝቶ መካሔድ ሲጀምር የመጀመረያውን ዋንጫ በማንሳት ቀዳሚ ክለብ ነው፡፡ በሳምንቱ ክለቦች መካከል የተደረገውን ውድድር ለማጠናቀቅ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ የጥሎ ማለፉንም ዋንጫ ደርቦ በመውሰድ የድርብ ድል ባለቤት ከሦስት አመት በኃላ በድጋሚ ሆነ፡፡ ይህን ዋንጫ በማንሳት ውጤታማ ሆኗል፡፡ በ 1993 የተካሔደውን ውድድር በሙሉ የበላይነት ሲያጠናቅቅ በሁለተኛው ዙር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ባጠቃላይ በማሸነፍ መሆኑ የወቅቱ የቡድኑን ስብስብ ጥንካሬ ያሳያል፡፡ አንዋር ያሲን፣ አንዋር ሲራጅ፣ ኤልያስ ጁሀር እና ወንድማማቾቹ ስምኦን አባይና ዮርዳኖስ አባይ የዚህ ቡድን አባለት ከነበሩት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ አመት 1993 ለመብራት ሀይል ልዩ አመት ነበር ማለት ይችላል፡፡ ከፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ በተጨማሪ የሦስትዮሽ ድል ባለቤት የሆኑበት ዓመት ነበር፡፡

ላለመውረድ የሚታገለው መብራት ሀይል 

የመብራት ሀይል እግር ኳስ ክለብ ውጤታማ ተብለው ከሚጠቀሱ የሀገሪቱ ክለቦች አንዱ ቢሆንም በቅርብ አመታት ግን ውጤት ርቆት ወደ ብሔራዊ ሊግ ላለመውረድ በመታገል ላይ ነው በተለይም በ 2001 እና 2002 የውድድር ዘመን በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ መጨረሻ አካባቢ በመሆን የመውረድ ስጋት አንዣቦበታል፡፡ የክለቡ ስብስብ ላለመውረድ ከሚፎካከራቸው ክለቦች ይልቅ የተሻለ ነው ቢባልም ውጤት ርቆታል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁን በመዝለቅ ከሚታወቁ ጥቂት ክለቦች አንዱ የሆነው መብራት ሀይል ወደ ብሔራዊ ሊግ ከወረደ በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል፡፡ 

መብራት በኢንተርናሽናል ውድድሮች 

መብራት ሀይል ሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ክለብ በመሆኑ ሦስት ጊዜ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድል አግኝቷል፡፡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ዋንጫን ካነሳ በኃላ በ1986 የአፍሪካ ሻምፒዮን ክለቦች ሻምፒዮና ተብሎ ይጠራ በነበረበት ወቅት ነው የተሳተፈው፡፡ በዚህ ውድድር በቅድመ ማጣሪያው የሩዋንዳ ኢዩሹ ስፖርትን 5ለ4 በሆነ ድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሎ ነበር፡፡ ይሁንና በአንደኛው ዙር ከኬንያው ጎርማሃያ ጋር ሦስት አቻ ተለያይቶ ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ሕግ ተበልጦ ወደ ሁለተኛው ዙር ሳያልፍ ቀርቷል፡፡  የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱን ተከትሎ በ 1991 ዳግም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ በኡጋንዳው ቪላ ኪጋሊ 7 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፎ ወጥቷል፡፡ ኪጋሊ ላይ 5 ለ 0 መሸነፉ ነበር የመልሱን ጨዋታ ያከበደበት በ 1999 ለሦስተኛ ጊዜ እድሉን ሲያገኝ በኬንያው አሰርያን ፈስታክ 3 ለ 1 ተሸንፎ ከቅድመ ማጣሪያው ደረጃ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

 ሌላው መብራት ሀይል የተሳተፈበት ካፍ ካፕ ተብሎ ይጠራ የነበረውና አሁን የተቋረጠው ውድድር ነው በ 1988 በሞዛምቢኩ ፎሮቪያርዮ 2 ለ 0 ተሸንፎ በአንደኛ ዙር ቀረ፡፡ በ 1990 የታንዛኒያው ምላንደግ ራሱን በማግለሉ ወደ ሁለተኛው ዙር ቢያልፍም በዛምቢያው ንቻንጋ ሬንጀርስ 2 ለ 1 ተሸንፎ ተሰናበተ፡፡ በ 1993 የታንዛኒያውን ምትብዋ ሹጋርን አሸንፎ ካለፈ በኃላ በሁለተኛው ዙር በአልጄርያው ጄ ኤስ ካቢልዬ ተበልጦ ወደ ሩብ ፍፃሜው ሳይልፍ ቀርቷል፡፡ 

 
 
 
 
 
EthioPL Table
RankClub Name PGDPTS
1St.George221940
2Dedebit231440
3Sidama Coffee23639
4Ethiopian Coffee23936
5Adama City23436
6Fasil City21132
7Hawassa City23331
8Woldya City23027
9Diredawa City24-427
10Defence Force25-827
11Arba Minch25-426
12Welayta Dicha27-1125
13Jimma abbabuna22-324
14Electric22-322
15A.A. City24-820
16Commercial Bank24-1518
Electric Players:
Electric Fixture :
Team Date Time
Electric Vs Commercial Bank April 13, 2017 9:00
Electric Vs Woldya City June 10, 2017 9:00
Hawassa City Vs Electric June 17, 2017 9:00
Electric Results:
HomeTeamScoreAwayTeam
Welayta Dicha0 - 0Electric
Electric1 - 1Arba Minch
Commercial Bank1 - 1Electric
Jimma abbabuna0 - 0Electric
Diredawa City2 - 1Electric
Electric1 - 1A.A. City
Dedebit2 - 0Electric
Fasil City0 - 0Electric
Electric0 - 0Adama City
Sidama Coffee1 - 1Electric
Electric2 - 1Welayta Dicha
Ethiopian Coffee0 - 0Electric
Electric0 - 1St.George
Electric1 - 2Defence Force
Woldya City1 - 1Electric
Electric2 - 0Hawassa City
Electric0 - 0Jimma abbabuna
Electric3 - 1Diredawa City
A.A. City0 - 0Electric
Arba Minch2 - 0Electric
Electric1 - 1Dedebit
Electric0 - 1Fasil City
Electric Players Goal Statistics x
Fitsum Gebremariam 9
Peter Okochuko 9
Dawit Estifanos 5
Adisu Negash 2
2
Fofana Ibrahim 2
Tesfaye Melaku 1
Biruk Ayele 1
Bereket Tessema 1
Sisie Hussien 1
Asalfew Mekonin 1
Hatamu Mengesha 1
 
 
Copyright© 2015 ethiofootball.com. All rights reserved!
Designed and Hosted by webPro